Welcome to the Apostolic Church International Fellowship Woodbridge, VA
ወደ ውድብሪጅ ቬርጂኒያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እንኳን ደህና መጡ
"Hear, O Israel: The LORD our God is one LORD" Deuteronomy 6:4
"እስራኤል ሆይ ስማ ፣ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው" ዘዳግም 6:4
Worship and Services
Our church welcomes everyone to experience spiritual growth and connection through various services.
Bishop Tibebu E Ayalew
The congregation is caught up in a genuine, soul-deep communion with the Divine. A true and heartfelt offering is ascending to God's throne.We are united, offering a worship that flows from the heart and the inner being.
ጉባኤው የሰማዩን አምላክ እውነተኛ በሆነና በነፍስ ደረጃ በሚደረግ ጥልቅ አምልኮ ሲያነግስ! ቅን እና ከልብ የመነጨ ምስጋና ወደ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን እየወጣ ሲያርግ! ሁላችንም በአንድ ልብ ሆነን ፣ ከውስጥ ማንነታችንና ከልባችን የሚፈልቀውን በመንፈስ የሆነ እውነተኛ አምልኮ ለእግዚአብሔር ስናቀርብ!
ጉባኤው የሰማዩን አምላክ እውነተኛ በሆነና በነፍስ ደረጃ በሚደረግ ጥልቅ አምልኮ ሲያነግስ! ቅን እና ከልብ የመነጨ ምስጋና ወደ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን እየወጣ ሲያርግ! ሁላችንም በአንድ ልብ ሆነን ፣ ከውስጥ ማንነታችንና ከልባችን የሚፈልቀውን በመንፈስ የሆነ እውነተኛ አምልኮ ለእግዚአብሔር ስናቀርብ!
Distinguished by his spiritual depth and pastoral grace, Bishop Tibebu shepherds the congregation with an unwavering commitment to faith and discipleship. Under his transformative leadership, the church has become a beacon of hope, inspiring members to actively engage with, uplift, and serve the surrounding community with love and excellence.ቢሾፕ ጥበቡ አያሌው የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛላቸውና የተባረኩ የቤተክርስቲያናችን መጋቢ ሲሆኑ ፡ ምዕመናንን በጽኑ እምነት ፣ በቅዱስ ቃልና በበሰለ መንፈሳዊ መሪነት ከማነጽ ባለፈ ፡ ቤተክርስቲያኗ በማህበረሰቡ ውስጥ ንቁ ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪና አርአያነት ያለው ተሳትፎ እንድታደርግ በታላቅ ቁርጠኝነት እየመሩ ይገኛሉ።
Solo performance that truly resonates: a heaven-opening song that stirs up the soul and revive the spirit of the congregation
በእውነት ወደ ውስጠኛው ማንነት ዘልቆ የሚገባ የብቸኛ ሰው (የሶሎ) አምልኮ፦ ሰማያትን የሚቀድ፣ ሰውን ከውስጥ የሚያናውጥ እና የቅዱሳኑን መንፈስ የሚያድስ ዝማሬ።
በእውነት ወደ ውስጠኛው ማንነት ዘልቆ የሚገባ የብቸኛ ሰው (የሶሎ) አምልኮ፦ ሰማያትን የሚቀድ፣ ሰውን ከውስጥ የሚያናውጥ እና የቅዱሳኑን መንፈስ የሚያድስ ዝማሬ።
Community and connection
Apostolic Church International Fellowship (ACIF) in Woodbridge, VA is an extended organ of the Apostolic Church Fellowship in North America (ACIFNA). We are a small church community with a big heart. Our mission is to follow Jesus by worshipping God, studying His Word, and serving our neighbors right here in Woodbridge, VA and in DMV area.
We are bible-based, simple faith, deeply connected, family-friendly, multicultural church, focusing on growing closer to God and each other. If you're looking for a place to ask questions and take your next steps in faith, you've found it.
መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ትስስር
የውድብሪጅ ቨርጂኒያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን አንድነት (ACIFNA) አካል የአጥቢያ ቤተርስቲያን ነው። ይህ አጥቢያ ገና ጀማሪ እንደመሆኑ ፣ ትንሽ እና አዳጊ ቤተክርስቲያን ቢሆንም ትልቅ ልብ ያላቸው ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ የተካኑ ብዙ ሰማያዊ ማኅበረሰብ ያሉት በተስፋ የተሞላ ቤተክርስቲያን ነው። ተልእኳችን እግዚአብሔርን በማምለክ፣ ቃሉን በማጥናት እና እዚሁ ስቴት እና በአካባቢው ጎረቤቶቻችንን በወንጌል በማገልገል ፣ ለእግዚአብሔር መንግስት እያዘጋጀን የኢየሱስ ክርስቶስን ተልእኮ መፈጸም ነው።
አጥቢያ ቤተክርስቲያናችን ፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ፣ ዘወርዋራ ያልሆነ እምነት ያለው፣ ጠንካራ ክርስቲያናዊ ግንኙነት ያለው፣ ቤተሰብ ተኮር፣ ብዙ ባህል ያላቸውን ሰዎች የሚያቅፍ፣ ከእግዚአብሔርና ከወገኖች ጋር በጥብቅ መቀራረብን ትኩረት ያደረገ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነው። የሕይወት ጎዳናዎትን ለማስተካከል ፣ ከሚመጣው ቁጣ አምልጠው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመቀላቀል የወሰኑ ሰው ክሆኑ ፣ ይህ ትክክለኛ ቦታ ነው። ጥያቄዎትን ይዘው ይምጡ! የእግዚአሔር ቃል መልስ አለው።