• Home / ዋናው ገጽ
  • About / ስለ እኛ
  • Contact Us / እኛን ለማግኘት
  • Resources / ክምችት
    • Books / መጽሐፍት
    • Magazines / መጽሔቶች
    • Sermons / ስብከቶች
    • Conferences / ኮንፈራንሶች
    • Articles / ጽሑፎች
    • Songs / መዝሙሮች

Apostolic Church International Fellowship in Woodbridge Virgina connecting members and visitors to church services, events, and community outreach initiatives.





በአሜሪካ ውድብሪጅ ቨርጂኒያ የሚገኘው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የአጥቢያውን አባላት እና ጎብኚዎችን ከቤተክርስቲያኑ አገልግሎቶችና ከመንፈሳዊ ዝግጅቶች ጋር ያገናኛል ፤ ማህበራዊ የተልዕኮ አገልግሎቱንም በጸሎት እና ወንጌልን በመስበክ ያከናውናል ።

What we believe in

እምነታችን

We believe that God is only One indivisible God.
By understanding from the Scriptures, we believe that God is one in divinity and personality; there is a single, indivisible divine person who has manifested in different ways or roles. We have the following Scriptural evidence: Deut. 6:4; “Hear, O Israel: The Lord our God is one Lord.” Isa.43:10-11; “Ye are my witnesses, saith the Lord, and my servant whom I have chosen that ye may know and believe me, understand that I am he: before me there was no God formed, neither shall there be after me. I, even I, am the Lord; and beside me there is no savior.” Isa. 45:21-22; “Tell ye, and bring them near; yea, let them take counsel together: who hath declared this from ancient time? Who has told it from that time? have not I the Lord? and there is no God else beside me; a just God and a Savior; there is none beside me. Look unto me, and be ye saved, all the ends of the earth: for I am God, and there is none else.” Hos. 13:4; “Yet I am the Lord thy God from the land of Egypt, and thou shalt know no god but me: for there is no savior beside me.” We believe that the Lord Jesus Christ is that only God of salvation manifest in the flesh to save us from our sins. We have the following Scriptural evidences: 1Tim. 3:16; “And without controversy great is the mystery of godliness: God was manifest in the flesh, justified in the Spirit, seen of angels, preached unto the Gentiles, believed on in the world, received up in to glory.” Mat. 1:18-23; “Now the birth of Jesus Christ was on this wise: When as his mother Mary was espoused to Joseph, before they came together, she was found with child of the Holy Ghost… for that which is conceived in her is of the Holy Ghost. And she shall bring forth a son, and thou shalt call his name JESUS: for he shall save his people from their sins. Now all this was done, that it might be fulfilled which was spoken of the Lord by the prophet, saying, Behold, a virgin shall be with child, and shall bring forth a son, and they shall call his name Emmanuel, which being interpreted is, God with us.” 1Tim. 1:15-17; “This is a faithful saying, and worthy of all acceptations, that Christ Jesus came into the world to save sinners … Now unto the king eternal, immortal, invisible, the only wise God, be honor and glory forever and ever, Amen.” Christ Jesus that came into the world to save sinners, we believe, died for our sins according to the scriptures; and that he was buried, and that he rose again the third day according to the scriptures. (1Cor. 15:3-4)
Baptism in the name of Jesus Christ for salvation.
Mark. 16:15-16 it says, “And he said unto them, Go ye into all the world, and preach the gospel to every creature. He that believeth and is baptized shall be saved; but he that believeth not shall be damned.” From this message, we can understand that; One gospel of salvation is sent to the whole world. That same gospel is to be preached to every human creature. The one who believes that gospel and be baptized shall be saved. Those who do not believe that gospel shall be damned. We believe that baptism in the name of Jesus Christ is also one of the essentials for salvation. We have got the following Scriptural evidences for this. Mar. 16:16 says, “…He that believeth and is baptized shall be saved.” Thus we believe that faith effects with baptism as well as when baptism is by faith. Faith in the gospel of Jesus Christ and baptism in his name inseparably work together for salvation. Acts 4:12 says, “Neither is there salvation in any other: for there is none other name under heaven given among men, whereby we must be saved.” Again in Acts 2:38 it says, “…be baptized every one of you in the name of Jesus Christ for the remission of sins,…” 1Pet. 3;20-21 says, “…when once the longsuffering of God waited in the days of Noah, while the ark was a preparing, where in few, that is, eight souls were saved by water. The like figure whereunto even baptism doth also now save us…” We believe baptism is essential for salvation for it is the way by which a man be born again from water according to John 3:3-6; it is the operation of God in which a man be circumcised by the circumcision of Christ according to Col. 2:11-12, and it is the way by which a man puts on Christ according to Gal. 3:27. We believe that even those who were baptized in other baptisms must be baptized again in the name of Jesus Christ for remission of their sins, or to be saved. According to Luke 24:47; Acts 2:38; 8:4-16; 10:1-3, vs. 43-48; 19:1-5 and 22:16, we believe that every human creature, without difference, must be baptized in the name of Jesus Christ for the salvation of their souls.
Receiving the Holy Sprit
The word of the Lord Jesus to Nicodemus in John 3:3-6 says, “Jesus answered and said unto him, Verily, Verily I say unto thee, except a man be born again, he cannot see the kingdom of God.. Verily, Verily, I say unto thee, Except a man be born of water and of the Spirit, he cannot enter into the kingdom of God. That which is born of the flesh is flesh; and that which is born of the Spirit is spirit.” From this word we can clearly understand that being born again from water and the Spirit is essential for the salvation of a human being. In John 3:6 it says, “That which is born of the flesh is flesh.” That means he/she is Adamic. The body, soul and spirit of every Adamic being is sinful and lost. Thus, the fallen nature of everyone needs regeneration in order to be saved. Tit. 3:4-5 says, “But after that the kindness and love of God our Savior toward man appeared, not by work of righteousness which we have done, but according to his mercy he saved us, by the washing of regeneration, and renewing of the Holy Ghost.” We believe, according to this word, that regeneration by baptism in water (in the name of Jesus Christ) and receiving the gift of the Holy Ghost are essentials for salvation. We also believe that for that reason the word of God in Acts 2:38 says, “…Repent, and be baptized every one of you in the name of Jesus Christ for the remission of sins, and ye shall receive the gift of the Holy Ghost,”
በስጋ በተገለጠው ፣ በአንድ አምላክ ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን
አዳኙ አምላክ አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ይህን ከቃሉ አረጋግጠን እናምናለን፡- ዘዳ.6÷4፡- “እስራኤል ሆይ÷ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡” ይላል፡፡ ኢሳ.43÷10-11፡- “ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ÷ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም፡፡ እኔ÷ እኔ እግዚአብሔር ነኝ÷ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም፡፡” ይላል፡፡ ኢሳ.45÷21-22፡- “…ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ÷ ከእኔም በቀር ማንም የለም፡፡ እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ÷ እኔ አምላክ ነኝና÷ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ፡፡” ይላል፡፡ ሆሴዕ 13÷4 “እኔ ግን ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም÷ ከእኔም በቀር ሌላ መድኃኒት የለም፡፡” ይላል፡፡ ይህ አንዱ አምላክ እኛን ከኃጢአታችን ለማዳን በሥጋ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ከቃሉ አረጋግጠን እናምናለን፡፡ 1ኛጢሞ.3÷16 “እግዚአብሔርን የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ÷ በመንፈስ የጸደቀ÷ ለመላዕክት የታየ÷ በአሕዛብ የተሰበከ÷ በአለም የታመነ÷ በክብር ያረገ፡፡” ይላል፡፡ ማቴ.1÷18-23 “የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበር፡፡ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ተገኘች፡፡ …ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና… ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፡፡ በነቢይ ከጌታ ዘንድ፡- እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል÷ ትርጓሜውም፡- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው፡፡” ይላል፡፡ 1ኛጢሞ.1÷15-17 “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ …ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን፡፡” ይላል፡፡ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም የመጣው ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሳ ብለን እናምናለን (1ኛቆሮ.15÷3-4)፡፡ ሰዎችም ሁሉ መዳንን የሚያገኙት በጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሥራ በማመን ብቻ እንደሆነ እናምናለን (1ኛቆሮ.1÷18-24)፡፡ ስለዚህ ለመዳን ይህን አንዱን አዳኝ አምላክ ማወቅና ማመን ያስፈልጋል፡፡ (የበለጠ ለማወቅ “በሥጋ የተገለጠ አንድ አምላክ” በሚል ርዕስ በቢሾፕ ደጉ ከበደ የተጻፈውን መጽሐፍ ያንብቡ)
ጥምቀት በጌታችን በኢየሱስ ርስቶስ ስም እንደሆነ እናምናለን
ጌታ ኢየሱስ ሐዋርያቱን የመዳን ወንጌልን እንዲሰብኩ ሲልካቸው የተናገራቸው ቃል በትኩረት መታየት ያለበት ነው፡፡ ቃሉ በማር.16÷15-16 ላይ፡- “እንዲህም አላቸው፡- ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡ ያመነ የተጠመቀም ይድናል÷ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡” ይላል፡፡ ከዚህ ቃል የምንረዳው፡- አንድ የመዳን ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ የተላከ መሆኑን፣ ይህ አንድ የመዳን ወንጌል ለፍጥረት (ለሰዎች) ሁሉ የሚሰበክ መሆኑን፣ ያንን ወንጌል የሚያምንና የሚጠመቅ እንደሚድን፣ ያንን ወንጌል የማያምን እንደሚፈረድበት ነው፡፡ ቀደም ሲል ለመዳን አዳኙን አንድ አምላክ ማወቅና ማመን እና ንስሐ መግባት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ስለሆነ ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸው ለመዳን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ ለመዳን ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ እንደሆነ የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ላይ ተመሥርተን ነው፡፡ በማር.16÷16 ላይ፡- “…ያመነ የተጠመቀም ይድናል” ስለሚል እኛ “ እምነት ከጥምቀት ጋር፣ ጥምቀት በእምነት ሲሆን ያድናል” ብለን እናምናለን፡፡ ወደ ጥምቀት የማያደርስ እምነትና በእምነት ያልሆነ ጥምቀት ሁለቱ ተለያይተው አይሠሩም፡፡ በሐዋ:ሥራ. 4÷12 ላይ፡- “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡” ስለሚል እኛ ጥምቀት የሚያድነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲከናወን ነው ብለን እናምናለን፡፡ በሐዋ:ሥራ. 2÷38 ላይ፡- “…ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ” የተባለውም ስለዚህ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በ1ጴጥ.3÷20-21 ላይ “ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግስት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡ ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል” ስለሚል በዚህም ቃል መሰረት እኛ “ ጥምቀት ያድናል” ብለን እናምናለን፡፤ በዮሐ.3÷3-6 መሠረት ጥምቀት ሰው ከውኃ ዳግመኛ የሚወለድበት፣ በቆላ.2÷11-12 መሠረት ሰው በእግዚአብሔር አሠራር በክርስቶስ መገረዝ÷ በእኛ ባልተደረገ መገረዝ የሚገረዝበት፣ በገላ.3÷27 መሠረት ሰው ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ ተጠምቆ ክርስቶስን የሚለብስበት ነው ብለን እናምናለን፡፡ በሐዋ:ሥራ. 19÷1-5 መሠረት ቀደም ሲል በሌላ ጥምቀት ተጠምቀው የነበሩትም ሰዎች ለኃጢአት ስርየት በጌታ በኢየሱስ ስም መጠመቅ ለመዳን ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ በመሆኑ እንደገና መጠመቅ ያስፈልጋቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ በሉቃስ 24÷47 ፣ በሐዋ:ሥራ. 2÷38፣ በሐዋ:ሥራ. 8 ÷4-16፣ በሐዋ:ሥራ. 10÷1-2፣ ቁ.43-48፣ በሐዋ;ሥራ. 19÷1-5፣ በሐዋ:ሥራ. 22÷16 መሠረት ያለ ልዩነት ለሰዎች ሁሉ (ለአይሁድም ለአሕዛብም) በጌታ በኢየሱስ ስም መጠመቅ ለመዳን ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ ነው ብለን እናምናለን፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን የመቀበል አስፈላጊነት እናምናለን 
ጌታ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የተናገረው ቃል በዮሐ.3÷3-6 ላይ፡- “ኢየሱስም መልሶ፡- እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው፡፡ …እውነት እውነት እልሃለሁ÷ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው÷ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡” ይላል፡፡ ይህ ቃል ሰው ለመዳን ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ እንደሚያስፈልገው ይገልጻል፡፡ ለመዳን ከውኃ የመወለድ ወይም ለኃጢአት ስርየት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የመጠመቅ አስፈላጊነት ቀደም ሲል ስለተገለጸ ከዚህ ቀጥሎ ከመንፈስ ስለመወለድ አስፈላጊነት ተገልïአል፡፡ በዮሐ.3÷6 እንደተጻፈው ከሥጋ (ከአዳም ዘር) የተወለደው ሁሉም ሥጋ (አዳማዊ) ነው፡፡ ሥጋውም፣ ነፍሱም፣ መንፈሱም በኃጢአት ምክንያት የረከሰና የሞተ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው በዳግም ልደት መዳን የሚችለው ከውኃ በመወለድ ብቻ ሳይሆን ከመንፈስም በመወለድ ነው፡፡ በቲቶ 3÷4-5 የተጻፈው ቃል፡- “ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ ÷ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ÷ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ስራ አይደለም፤” ይላል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት እኛ ሰው የሚድነው ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብ (በጌታ በኢየሱስ ስም ጥምቀት) እና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በሐዋ:ሥራ. 2÷38 ላይ፡- “ንስሐ ግቡ÷ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡” የተባለውም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መቀበል ለመዳን ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ ስለሆነ ነው ብለን እናምናለን፡፡

We use cookies to enable essential functionality on our website, and analyze website traffic. By clicking Accept you consent to our use of cookies. Cookies and Privacy Policy.

Your Cookie Settings

We use cookies to enable essential functionality on our website and analyze website traffic. For more information, read our Cookies and Privacy Policy.

Cookie Categories
Essential

These cookies are strictly necessary to provide you with services available through our websites.

Analytics

These cookies collect information that is used in aggregate and in an anonymized form to help us understand how our website is being used and how effectively our site is performing.